|
Thursday, 25 June 2009 |
Sunday, 21 June 2009 Reporter
ከሐረር 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የሶፊ ያህያ አድባር ሲሆን የመጀመሪያው የቁርአን ማስተማሪያ ትምህርት ቤት ነበር፡፡ የአብዱልቃድር ጄይላን እና ኡሚ ኮይዳ መስጊድም ከሐረር 12 ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል፡፡
የሐረር ከተማ የመጀመሪያው ንፁህ የቧንቧ ውሃ ከመጀመሪያው የቁርአን ትምህርት ቤት ጎን የተገኘ ሲሆን የሶፊ ያህያን ጥሩ ተግባር ለማስታወስ በእሳቸው መቃብር ላይ አድባሩ ተገንብቷል፡፡
ከሶፊ መንደር 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የቡርቃ መንደር ሲሆን፣ በመንደሩ 1234 ዓመት እድሜ ያለው ኡሚ ኮዳ መስኪድ ይገኛል፡፡ የአካባቢው ኅብረተሰብ መስኪዱን ለየት የሚያደርገው የዚህ ዓይነት መስኪድ በቱርክና በኢራቅ ብቻ የሚገኝ መሆኑ ነው ብለው ያምናለሁ፡፡ የኡሚ ኮዳ መስኪድ ስድስት እንደ ሚሳይል ወደ ላይ የሚያዩ መናራ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት አንዱ ብቻ የቀረ ሲሆን፣ በጥሩ ቅርጽ የተሰሩ የመስኪዱ ቋሚዎችና ፀሎትን የሚመሩት (ኢማም) የማሰገጃ ቦታ የኡሚ ኮዳን መስኪድ ከሌሎች ለየት ያደርገዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ኢንዱስትሪ ትራንስፖርት ንግድና ቱሪዝም ቢሮ፤ ሐረሪ |
|
|
|
<< Start < Prev 1 2 Next > End >>
|
| Results 1 - 9 of 14 |